Our Mission

የኢትዮጵያ ቀን ዓላማዎች

  • በመላው ስዊዘርላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያንን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች በየዓመቱ እየተገናኙ የሚያከብሩትን የጋራ በዓል ማዘጋጀት፣
  •  የኮሚዩኒቲዎች የእርስ በእርስ ትውውቅ እንዲፋፋ ማቀራረብ፣
  • ሕጻናት የሀገራቸውን ባህልና መሰል እሴቶችን እያዩ እንዲያድጉ እድሎችን ማመቻቸት፣
  • በመካከላችን ያሉ ማንኛውም ዓይነት ልዩነቶቻችንን በእኩልነት እያየን በመከባበር የምንኖርበትን ባህል ማበልጸግ፣
  • የሀገራችንን ባህል እና ወግ ለስዊስ ዜጎች እያስገነዘብን በመካከላችን ሊኖር የሚገባውን ቅርርብ ማጠንከር፣
 
እስካሁን ምን ምን አከናወንን ?

Our Vision /የኢትዮጵያ ቀን ራዕይ/

የኢትዮጵያ ቀን ዋና ራዕይ በመላው ስዊዘርላንድ ተበታትነን የምንገኝ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በየዓመቱ እንድንገናኝ እና እንድንተዋወቅ በማድረግ በመካከላችን ወዳጅነታቸው እንዲፋፋ ማበረታታት ነው።  ለዚህም በዓመታዊ ፌስቲቫል ማህበራትን አቅፎ ይሰራል፣ የዓመቱን ምርጥ ሰውና የዓመቱን ምርጥ ድርጅት ይሸልማል፣ ዕውቅናም ይሰጣል።

Testimonial 1

You did well today. I am an Ethiopian and i love Ethiopia for ever. Unity is the only way for Ethiopian, so that let us go ahead together. God bless Ethiopia.

Testimonial 2

በጣም ቆንጆ ዝግጅት ነበር። እግዚአብሔር አምላክ ሁሉንም አዘጋጆች ይባርካችሁ። ኢትዮጵያዊነትን አይቼበታለሁ። መዋደድን፣መከባበርን፣ ፍቅርን አይቼበታለሁ። በበለጠ ደግሞ ለልጆች ባህላችንን፣ቋንቋችንን ማስተዋወቅ። በቲያትርም ሆነ በድራማ፣ በፋሽን ሾው ለማሳየት ያደረጋችሁት የሚደነቅ ነው። ተተኪዎች እነሱ ስለሆኑ። Super !!

Testimonial 3

ውድ የሀገሬ ልጆች አጀማመራችሁ የሚበረታታ ነው። ይህ የኢትዮጵያ ቀን በየዓመቱ እዚሁ በርን ከተማ ላይ በቋሚነት ቢዘጋጅ መልካም ይመስለኛል። በርቱ ተበራቱ። ወጣቱንም አሳትፉት፣ አበረታቱት ።

Reach Out To Us

.

Ethiopia Day In Swiss  is a non-political, non-profit, independent, community-based organization that is established to preserve and promote Ethiopian cultural heritage, thereby adding a positive impact to the host country -Switzerland.