Testimonials

Testimonial 1

Dear Organisers,
I would like to sincerely thank you for organising the Ethiopian Day in Bern. This was my first time attending, and I found it to be a truly beautiful and memorable occasion. It was clear that a great deal of thought and effort went into making the programme enjoyable, and it was wonderful to see so many people from different backgrounds come together and share in the joy of the day. The turnout was impressive, and I am confident that the gathering will continue to grow in the years ahead. One of the strongest messages I take away from this event is the power of working together. As our proverb reminds us, “when cobwebs unite, they can tie down a lion”—or, in English, “many straws may bind an elephant.” The celebration was a living example of this spirit of unity, and it gives me great hope for what we can achieve collectively. Please continue with your wonderful efforts. You have shown our community that with will and dedication, success is always possible. I will gladly support this good cause and do my part in serving our community. You have left a lasting impression on me, as I am sure you have on many others, and I wish you every success in all that you do.
Beide Mariam, from Basel 30 Aug. 2025

Testimonial 2

Dear Awraris and team.
Mein and family contributions were very minimal. The event was organized very well. Surprisingly, you organized each part to the detail so that last-minute mistakes are avoided. I am pleased to see a lot of Ethiopians and friends of Ethiopia from all corners. You made a very good mechanism to reach all these people. I met even a couple who came from Montepillar, France. Once again, thank you very much for bringing us all together. The 4th Ethiopia Day is a remarkable one.
Zerihun Tadelle (prof.) from Bern 30 Aug. 2025

Testimonial 3

የተከበራችሁ ውድ የኢትዮጵያ ቀን አዘጋጆች ድካም እንደለቀቃችሁ ተስፋ አደርጋለሁ 👏👏👏 ኑሩልኝ ክበሩልኝ ጉልበታችሁ ይባረክ ብዙ ተባዙልን 🙏🙏 በመካከላችሁ ያለው የስራ መንፈስ አብሮነት ቅንነት መተሳሰብ መደማመጥ እና መከባበሩ በመላው ኢትዮጵያዊ ልብ ዉስጥ ይጋባ የሚለው ምኞቴ ነው🙏🙏 እጅግ በጣም አስደሳች ቀን ነበር 🙏🙏🙏🙏በጣም በጣም እናመሰግናለን 🙏🙏🙏ለዛሬ ዓመት ከቁጥር ሳንጎል በዝተን በጤና በሰላም ያድርሰን 🙏🙏🙏
💚ምንጊዜም እማማ ኢትዮጵያችን ትቅደም💚
Solome from Bern 30 Aug. 2025

Testimonial 4

እጅግ የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ቀን አዘጋጆች እንደየማዕረጋችሁ፣- ለስጣችሁኝ ፍፁም ፍቅር ከልቤ አመሰግናለሁ🙏 ትናንት ከወገኔ ጋር ሀዘኔን ተጋራሁ - ደግሞም በሰጣችሁኝ ክብር ተፅናናሁ፣ ይህ ሁለት የገዘፈ ኹነት በአንድ ሥፍራ በዚህ መልኩ በሕይወት መንገዴ ላይ ይከናወናል ብዬ አስቤ አላውቅም - ግን ሆነ! ትናንት የሰጣችሁኝ የዕውቅና ሽልማት በሕይወት ዘመኔ የመጀመሪያው መሆኑ ብቻ ሳይሆን ከምሳሳላት ሀገሬ ጋር የተቆራኘ በመሆኑ ልዩ ትርጉም አለው። ለሰጣችሁኝ ልዩ ክብር እና ሽልማት ደግሜ ደጋግሜ አመሰግናለሁ🙏 ስለኢትዮጵያ የምትደክሙትን ድካም እግዚአብሔር ይቁጠርላችሁ! የኢትዮጵያ አምላክ ይጠብቃችሁ! ኑሩልኝ🙏 በማንኛውም ሁኔታ ከጎናችሁ ነኝ.. እክባሪያችሁ!
Kidist from Witzikon 30 Aug. 2025

Testimonial 5

You did well today. I am an Ethiopian and i love Ethiopia for ever. Unity is the only way for Ethiopian, so that let us go ahead together. God bless Ethiopia.

Testimonial 6

ውድ የሀገሬ ልጆች አጀማመራችሁ የሚበረታታ ነው። ይህ የኢትዮጵያ ቀን በየዓመቱ እዚሁ በርን ከተማ ላይ በቋሚነት ቢዘጋጅ መልካም ይመስለኛል። በርቱ ተበራቱ። ወጣቱንም አሳትፉት፣ አበረታቱት ።

Testimonial 7

በጣም ቆንጆ ዝግጅት ነበር። እግዚአብሔር አምላክ ሁሉንም አዘጋጆች ይባርካችሁ። ኢትዮጵያዊነትን አይቼበታለሁ። መዋደድን፣መከባበርን፣ ፍቅርን አይቼበታለሁ። በበለጠ ደግሞ ለልጆች ባህላችንን፣ቋንቋችንን ማስተዋወቅ። በቲያትርም ሆነ በድራማ፣ በፋሽን ሾው ለማሳየት ያደረጋችሁት የሚደነቅ ነው። ተተኪዎች እነሱ ስለሆኑ። Super !!

Testimonial 8

ይህን ሀሳብ አስቦ ኃላፊነት ወስዶ ይህንን ውብ የሆነ ዝግጅት ላዘጋጃችሁት አክብሮቴ ከፍ ያለ ነው። እግዚአብሔር ያክብራችሁ።

Testimonial 9

በተደረገው ነገር ደስ ብሎኛል። ይህ ፕሮግራም ተጠናክሮ ይቀጥል ዘንድ መልካም ምኞቴ ነው። እ/ር መሳካትን መከናወንን ለሁላችንም ያድርግልን። እግዚአብሔር ይባርካችሁ።

Testimonial 10

ጥቂት የማይባሉ የውጪ ዜጎች አብረውን ነበሩ። በጋብቻ፣ በተለያየ ምክንያት ከትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር የተቆራኙ፣ ይህ ሊደነቅ ይገባል።

.

Ethiopia Day In Swiss  is a non-political, non-profit, independent, community-based organization that is established to preserve and promote Ethiopian cultural heritage, thereby adding a positive impact to the host country – Switzerland.

[contact-form-7 id=”550f8aa” title=”New Contact”]