Who We Are
Ethiopia Day In Swiss is a non-political, non-profit, independent, community-based organization that is established to preserve and promote Ethiopian cultural heritage, thereby adding a positive impact to the host country -Switzerland.
የኢትዮጵያ ቀን አመሰራረት
በቅድሚያ ከኦክቶበር 19/2019 አንስቶ እስከ 2021 ባለው ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ የበርን ቻፕተርን በኢትዮጵያውያን ሙሉ ፈቃድ ስራውን ስንመራ የነበርነው አባላት በጊዜ ሂደት የቻፕተሩን ስራ ማካሄድ የማንችልበት ደረጃ ላይ ደረስን። በዚህ ተጨባጭ ሁኔታ አስገዳጅነት ዓመታዊው በዓላችን እንዳለፈው ጊዜ የትረስት ፈንዱን መሰረታዊ ዓላማዎች ከማሳወቅና ከማስፈጸም ይልቅ ሁላችንንም በኢትዮጵያዊነት መንፈስ የሚያሰባሰባስብና የሚያቀራርብ እንዲሆን የጸና እምነት አደረብን። በዚህ መነሻነት የኢትዮጵያን ቀን ዓላማና ራዕይ በጽሁፍ አስፍረንና ስያሜውን ለደጋፊዎቻችን አሳውቀን ቅዳሜ ኦገስት 20/2022 የመጀመሪያውን የኢትዮጵያን ቀን በዓላችንን አክብረናል። ይሁን እንጂ ብዙዎች የሚያውቁን በኢዲቴኤፍ የቻፕተር አስተባባሪነታችን በመሆኑ « እነማን ናችሁ ? » የሚል ጥያቄ በማንሳታቸው በፍሪቡርግ ማራቶን የኢትዮጵያ ሬስቶራንት የእራት ምሽት አዘጋጅተን ጥሪያችንን አክብረው ለተገኙ እንግዶቻችን July 16/2023 የበኩላችንን ማብራሪያ ሰጥተናል። አያይዘንም 2ኛውን የኢትዮጵያ ቀን ኦገስት 26 ቀን 2023 በደማቅ ሁኔታ አክብረናል።
ከቻፕተር ወደ Ethiopia-Day ለተደረገው ሽግግር ያለፍንባቸው መንገዶች
የበርን ቻፕተር እንደማንኛውም ቻፕተር ሁሉ በኢዲቲኤፍ የሥራ አመራር ቦርድ እውቅና ተሰጥቶት የሚሰራ እንደመሆኑ ከደጋፊዎቹ የሚደርሱትን ጥያቄዎች ለቦርዱ እየላከ ማብራሪያና ምላሽ እንዲሰጠው መዋቅሩን የጠበቀ ሂደትን ሲከተል ቆይቷል። ሆኖም ግን February 4, 2022 እና April 8, 2022 በኢሜይል ያቀረብናቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች በቦርዱ ችላ በመባላቸው ጉዳዩን በስልክ ለማጣራት ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም። ይህም ሆኖ ግን በበኩላችን ሕጋዊነትን ከተላበሰው አካሄዳችን ሳንወጣ ቆይተናል።
ጉዳዩን በድጋሚ በመረመርንበት ወቅት፣
- ባሳለፍናቸው ረዘም ያሉ ጊዜያት ውስጥ ከቦርዱ ምንም ዓይነት ምላሽ አለማግኘታችን በእጅጉ አሳዝኖናል።
- አልፎ አልፎ በሚቀርቡት የኢዲቴኤፍ የሥራ ሪፖርቶች ውስጥ የቦርዱን እና የቻፕተሮችን መዋቅራዊ ትስስር አስመልክቶ አንዳችም መግለጫ አለመሰጠቱ ቻፕተሮችን ያገለለ አካሄድ እየተተገበረ መሆኑን ልናስተውል አስችሎናል።
- የዲያስፖራው ማህበረሰብ ለቻፕተሮች የሚያደርገው ድጋፍ በከፍተኛ ሁኔታ እንደቀነሰ በሚታይበት ወቅት ቦርዱ ከቻፕተሮች ጋር በትስስር አለመስራቱ እንደቻፕተር ልንቀጥል አላስቻለንም።
ስለሆነም በቦርዱ በተሰጠን እውቅና መሰረት በበርን እና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለኢዲቴኤፍ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉ « የበርን ቻፕተር » በሚል መጠሪያ ስንፈጽም የቆየነውን የማስተባበርና የማነቃቃት ሥራ የማንፈጽም እና የበርን ቻፕተርም ከአራት የሥራ ዓመታት በኋላ የፈረሰ መሆኑን November 19, 2023 ለቦርዱ አሳውቀናል። ከዚያም ማህበረሰባችንን ለማገልገል ባለን ተነሳሽነት የኢትዮጵያን ቀን ያለ አንዳች የዘርና የፖለቲካ እንዲሁም የሃይማኖት ልዩነት ሁሉን አስተባብረን እና እጅ ለእጅ አያይዘን በየዓመቱ የምናከብረው የአንድነት በዓላችን ሆኖ እንዲቀጥል ወስነን የኢትዮጵያ ቀን መስርተን በመንቀሳቀስ ላይ እንገኛለን።
Reach Out To Us
.
Ethiopia Day In Swiss is a non-political, non-profit, independent, community-based organization that is established to preserve and promote Ethiopian cultural heritage, thereby adding a positive impact to the host country -Switzerland.